peoplepill id: kalbum
K
3 views today
4 views this week
The basics

Quick Facts

Gender
Male
The details (from wikipedia)

Biography

ካልቡም በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ የኪሽ 2ኛው ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ነበረ። የማማጋል (መርከበኛው) ልጅ ሆኖ ዘመኑ ለ195 (ወይም በ2 ቅጂዎች ለ135) አመታት እንደ ቆየ ሲል ይህ ግን ትክክለኛ አይመስልም። ከአዋን (ኤላም) ነገሥታት ቀጥሎ ኪሽ ላዕላይነቱን እንደ ያዘ ይለናል። በኪሽ የነገሡ ንጉሦች 1) ሱሱዳ የሱፍ ጠራጊ፣ 2) ዳዳሲግ፣ 3) ማማጋል መርከበኛው፣ 4) ካልቡም የማማጋል ልጅ፣ 5) ቱጌ፣ 6) መን-ኑና የቱጌ ልጅ፣ 7)...(?) 8) ሉጋል-ጙ ናቸው ይለናል።ዳሩ ግን ለነዚህ ነገሥታት ሁሉ አንዳችም ሌላ ቅርስ ገና አልተገኘም። መጀመርያ 3 ስሞች የካልቡም ቅድመ-አባቶች ይሆናሉ፣ እንጂ ንጉሳዊ ስሞች አይመስሉም። ኪሽ በዚህ ወቅት ላዕላይነቱን ከያዘ ቅርስ ባለመገኘቱ ዘመኑ አጭር መሆን (ምናልባት 2274-2243 ዓክልበ. ግድም) አለበት። ከካልቡም በኋላ የተዘረዘሩ ስሞች በሱመር ላዕላይ ነገሥታት ሳይሆኑ ምናልባት የከተማው ከንቲቦች ብቻ ነበሩ። ከኪሽ በኋላ የሐማዚ ንጉሥ ሃዳኒሽ እንደ ተነሣ ዝርዝሩ ይጨምራል።

ከኪሽ 2ኛ ሥርወ መንግሥት ሁሉ የ1 ንጉሥ ስም ምናልባት በቅርስ ሊታይ ይችላል። በ1962 ዓ.ም. ሊቁ ቶርኪልድ ያቆብሰን እንደ መሰለው፣ በላጋሽ ንጉሥ ኤአናቱም «የአሞራዎች ጽላት» ላይ በአንድ ቦታ የኪሽ ንጉሥ በኤአናቱም ጦር ጫፍ ላይ ተቀርጾ ሲያሳይ ጽሕፈቱ ምናልባት «የኪሽ ንጉሥ ካልቡም» ይላል።

  1. ^ Thorkild Jacobsen, Toward the image of Tammuz and other essays on Mesopotamian history and culture 1970, p. 393.
ቀዳሚው
የአዋን ንጉሥ
የሱመር (ኒፑር) አለቃ
2274-2243 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
የሐማዚ ንጉሥ ሀዳኒሽ
ቀዳሚው
ማማጋል፣ መርከበኛው
የኪሽ ንጉሥ
2274-2243 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ቱጌ
The contents of this page are sourced from Wikipedia article. The contents are available under the CC BY-SA 4.0 license.
Lists
Kalbum is in following lists
comments so far.
Comments
From our partners
Sponsored
Kalbum
arrow-left arrow-right instagram whatsapp myspace quora soundcloud spotify tumblr vk website youtube pandora tunein iheart itunes