peoplepill id: tsehaye-yohannes
TY
Ethiopia
2 views today
2 views this week
The basics

Quick Facts

Places
Work field
Gender
Male
Instruments:
The details (from wikipedia)

Biography

ፀሐይ ዮሐንስ (፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ተወለደ) የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ሲሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራወችንበማቅረብ ይታወቃል።

የሕይወት ታሪክ

ፀሐይ ዮሐንስ በ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. በኤርትራ ክፍለ ሀገር አሥመራ ከተማ ተወለደ። ፀሐይ ከአባቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት የሙዚቃ ችሎታውን ለማዳበር ቻለ። የ፭ኛ ክፍል ተማሪ እያለ በአብዮቱ ወቅት ፷ ሺህ ተማሪዎች ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለዕድገት በሕብረት ዘምተው ሳለ «በርታ ዘመዴ ዘማቹ ጓዴ» የተሰኘው የመጀመሪያውን ሙዚቃ ለሕዝብ በማቅረብ በወቅቱ ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል።

ከዚያም መሀይምነትን ለማጥፋት የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ በታወጀበት ጊዜ «ማንበብና መፃፍ» የተሰኘው ዘፈኑ በጣም ቀሽቃሽና አስተማሪ ስለነበር ፀሐይን ይበልጥ እንዲታወቅ አድርጎታል።

ከእነዚህም ማህበራዊ ሕይወትን ከሚገልፁት በተጨማሪ በ፲፱፻፸፭ ዓ.ም. ካሰማቸው ዘፈኖቹ ውስጥ «ፍንጭትዋ»፣ «ያዝ ያዝ» እና «ጡር ነው» የተሰኙት በሕዝቡ ዘንድ ውዴታን ያገኙ ነበሩ። ፀሐይ አሁንም ቢሆን የተለያዩ ዜማዎችን በመዝፈን በሕዝቡዘንድ ከፍተኛ አድናቆት ያለው አርቲስት ነው።

የሥራዎች ዝርዝር

  • ፲፱፻፸፬ተይ ሙኒት
  • ፲፱፻፸፭ፍንጭትዋ
  • ፲፱፻፸፯ሳብ ሳም
  • ፲፱፻፸፱ጡር ነው
  • ፲፱፻፹፪ተባለ እንዴ
  • ፲፱፻፹፭ኢትዮጵያ
  • ፲፱፻፹፱ያላንቺማ
  • ፲፱፻፺፪ጀመረች
  • ፲፱፻፺፬ለትንሽ
  • ፲፱፻፺፱ሳቂልኝ

ማጣቀሻዎች

The contents of this page are sourced from Wikipedia article. The contents are available under the CC BY-SA 4.0 license.
Lists
Tsehaye Yohannes is in following lists
comments so far.
Comments
From our partners
Sponsored
Credits
References and sources
Tsehaye Yohannes
arrow-left arrow-right instagram whatsapp myspace quora soundcloud spotify tumblr vk website youtube pandora tunein iheart itunes