peoplepill id: tamrat-molla
TM
Ethiopia
1 views today
3 views this week
The basics

Quick Facts

Places
Work field
Gender
Male
Birth
Place of birth
Gondar
Death
Age
69 years
The details (from wikipedia)

Biography

ታምራት ሞላ

ታምራት ሞላ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ሲሆን ብዙ ዘመናዊና ባህላዊ የሙዚቃ ስራወችንበማቅረብ ይታወቃል። በ፳፻ ዓ.ም የካንሰር በሽታ የተገኘበት ድምጻዊ ታምራት በህክምና ከህመሙ ሙሉ በሙሉ እንደ ተሻለው አሳውቆ የነበረ ቢሆንም ህመሙ እንደገና አገርሽቶበት በተወለደ በ፮፱ አመቱ በየካቲት ፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የቀብር ሥነ ሥርዓቱም በዕለቱ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተሰቦቹ ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ ፣ የሙያ አጋሮቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት ተፈጸሟል ።

የህይወት ታሪክ

ታምራት ሞላ በ፲፱፻፴፮ ዓ.ም. በጎንደር ክ/ሀገር ተወለደ። ታምራት የ፩ኛ ደረጃ ትምህርቱን እዚያው ጎንደር ከጨረሰ በኋላ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አድቬንቲስት ሚስዮን ትምህርት ቤት በመግባት ትምህርቱን ተከታተለ። ከ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. በቀድሞ ክብር ዘበኛ በወታደርነት በመቀጠር እስከ ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ጃዝ፣ ሳክስፎንና ሌሎችንም የሙዚቃ መሳሪያዎች መጫወት ጀመረ። በድምፁም ጭምር ስሜቱን ለማርካት በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. በምድር ጦር ኦርኬስትራ ተቀጠረ።

የሥራዎች ዝርዝር

ታምራት ለመጀመሪያ ጊዜ ካዜማቸው ዘፈኖቹ «ታምሜ ተኝቼ» እና «ዘውትር ብርቅነሽ» የተሰኙትን ዘፈኖቹን ለመጀመሪያ ጊዜ በመድረክ ላይ ሲያሰማ በተመልካቾች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፈውለት ነበር።

ታምራት እስካሁን ድረስ የዘፈናቸው ዘፈኖች በርካታ ቢሆኑም «አስታውሺኝ»፣ «መሞት አለ ለካ»፣ «የለችም» እና «ጊዜው ለጨነቀው» የተሰኙት ዜማዎቹ የተዋጣላቸው ከመሆናቸው ባሻገር በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ያላቸው ናቸው።

ታምራት ከነዚህ ስራዎች በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ በአንታራም ግጥም በተሞላው «ሰበቡ» በተሰኘ ዘፈኑ ይታወቃል።

አልበሞች

  • ፲፱፻፺፯ ዓ.ም. ተረት ሆኖ ቀረ

ማጣቀሻዎች

The contents of this page are sourced from Wikipedia article. The contents are available under the CC BY-SA 4.0 license.
Lists
Tamrat Molla is in following lists
comments so far.
Comments
From our partners
Sponsored
Credits
References and sources
Tamrat Molla
arrow-left arrow-right instagram whatsapp myspace quora soundcloud spotify tumblr vk website youtube pandora tunein iheart itunes