peoplepill id: merry-armde
MA
Ethiopia
1 views today
1 views this week
Merry Armde
Ethiopian singer

Merry Armde

The basics

Quick Facts

Intro
Ethiopian singer
Places
Work field
Gender
Female
Instruments:
The details (from wikipedia)

Biography

ሜሪ አርምዴ የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ስትሆን ባህላዊ ዘፈኖችን በወፈረ ድምጽበማቅረብ ትታወቃለች።ማርታ አሻጋሪም ከሜሪ አርምዴ ጋር ተመሳሳይ ድምጽ እንዳላት ይነገራል።

የህይወት ታሪክ

ሜሪ አርምዴ

----------------

-

ቤተሰቦቿ ያወጡላት ስም ሜሪማ የሚባል እንደነበር ይነገራል፡፡ ኋላ ላይ ዘመናዊነትን ስትነግሥበትና ፒያሳን ስትደምቅበት በራሷ ጊዜ ስሟን ሜሪ ብላ አስተካከለቸው፡፡

-

ሜሪ የተወለደችው በ1910 ዓ. ም.  በአዲስ አበባ ከተማ ዶሮ ማነቂያ ከሚባለው ሰፈር ነው፡፡

-

ቤተሰቦቿ ፈረንሳይኛን የተማሩ ሲሆኑ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ይሰሩ እንደነበር ሜሪ በ1973 ዓ. ም.  ለኢትዮጵያ ሬዲዮ በሰጠችው ቃለ መጠይቅ ላይ ተናግራለች፡፡

-

ምክንያቱ ባይታወቅም ሜሪ ገና በልጅነቷ አዲስ አበባን ለቃ ወደ ራያ ኮረም የሚባል ቦታ ሄዳለች፡፡ የልጅነት ጊዜዋንም በዚያው አሳለፈች፡፡

-

ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር ሜሪ የ13 ዓመት ልጅ ነበረች፡፡ መዝፈን፣ ማንጎራጎርም በዚያ ወቅት ጀምራለች፡፡

-

አምባላጌ ላይ የኢትዮ - ጣሊያን ጦርነት ሲጧጧፍ ሜሪ ብላታ ኅሩይ ከተባሉ አርበኛ ጋር አብራ ዘምታ ነበር፡፡

-

የአምባላጌውን እልህ አስጨራሽ ጦርነትን ጨምሮ ሌሎችም በአርበኞችና ፋሽስት ጣሊያን መካከል የሚደረግን ፍልሚያ በቅርበት አይታለች፡፡

-

በአንድ አውድ ላይም እግሯን ተመትታ የጦርነትን ዋጋ ከፍላለች፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥም ግን በእንጉርጉሮ ፣ በዘፈንና ሽለላዋ የአርበኞቹ የደስታ ምንጭ ነበረች፡፡

1. ዘመናዊ ዳንስ

2. ዘመናዊ የልብስ ስፌት

3. የፀጉር ተኩስ ስራ  ሙያዎች

በአዲስ አበባ ሜሪን ቀደምትና ታዋቂ አድርገዋታል ፡፡

-

በዚያ ላይ ታንጎራጉራለች፣ ክራር ትጫወታለች፣ የዳንስ ቤት ከፍታለች፡፡  በወቅቱ ስላልተለመደ ብዙዎች ባይወዱላትም የፀጉር ተኩስ ስራን ለብዙዎች ቀስ በቀስ እንዲወዱትና እንዲለምዱት አድርጋለች፡፡ በዚህም ሜሪ በከተማው ዝናዋ የናኘ ነበር፡፡

የስራ ዝርዝር

ማጣቀሻወች

The contents of this page are sourced from Wikipedia article. The contents are available under the CC BY-SA 4.0 license.
Lists
Merry Armde is in following lists
comments so far.
Comments
From our partners
Sponsored
Merry Armde
arrow-left arrow-right instagram whatsapp myspace quora soundcloud spotify tumblr vk website youtube pandora tunein iheart itunes