Kebbede Mikael
Quick Facts
Biography
ከበደ ሚካኤል (1909-1991) በደብረ ብርሃን ከተማ፣ ገርም ገብርኤል አጥቢያ ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፱ ዓ.ም.ተወለዱ። ወደ አዲስ አበባ እንደ መጡ መጀመሪያ በአሊአንስ ኢቲዮ-ፍራንሴዝ በኋላም በላዛሪስት ሚሲዮን ትምህርታቸውን ተከታተሉ። የሼክስፒርን ሮሜዎና ዡልየትን ማክቤዝን በመተርጎም እውቅናን ለማትረፍ ችለዋል።
ሌሎች ታዋቂ የትርጉም ሰራዎች መሃል፦
- ከይቅርታ በላይ በሚል አርእስት ከBeyond the Pardon በ M.Clay የተተረጎመው ሊጠቀስ የቻላል።
ከበደ ሚካኤል 30 ገደማ መፃሕፍትን ፅፈዋል። ከበደ ሚካእል ካበረከቷቸው የቴአትር ስራዎች
- የትንቢት ቀጠሮ
- የቅጣት ማእበል
- ካሌብ
- ሃኒባል
ይገኙባቸዋል።
ከበደ ሚካኤል በርካታ የስነ ጽሁፍ ስራዎች ባለቤት በመሆናቸው በተለይም ለልጆች ትምህርት አዘል ጽሁፎችን የግጥም የፈጠራ ስራዎችን ቅኔዎችን በስፋት በማበርክታቸው በኢትዮጵያ የስነጽሁፍ መድረክ ገናና ከሆኑት ደራሲዎች አንዱ ናቸው። ከነዚህም መሃል፦
- ታሪክና ምሳሌ ፩
- ታሪክና ምሳሌ ፪
- የህሊና ብርሃን
- የቅኔ ውበት (በ ......... ዓ.ም. ታተመ/ተጻፈ።)
- ጃፓን እንዴት ስለጠነች (በ ....... ዓ.ም. ታተመ/ተጻፈ።)
- ታላላቅ ሰዎች (በ ........ ዓ.ም. ታተመ/ተጻፈ።)
- የሥልጣኔ አየር (በ ......... ዓ.ም. ታተመ/ተጻፈ።)
ሊጠቀሱ ይችላሉ።
የሰዎች ስነ ምግባር ላይ የማተኮርና ምክር አዘል መልእክቶችን የማስተላለፍ ዝንባሌአቸው በአብዛኛው ስራቸው ላይ ይንጸባረቃል።
ዘመናዊት ኢትዮጵያን ለማደርጀት በተደረገው ትግል በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉ እኒህ ፈላስማ፥ ባለቅኔ፥ ጸሐፌ-ተውኔት፥ ደራሲና አንጋፋ ጋዜጠኛ ፥ 'የቀለም ሰው' በሀገራችን የመጀመሪያ የነበረውን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሽልማት ድርጅት በቀዳሚነት የተቀበሉ ሲሆን፣ አዲስ ትውልድ ላፈራ ስብእናቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም. በሥነ ጽሑፍ የክብር ዶክቶሬት ዲግሪ ሸልሟቸዋል። በተረፈም ከፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሶቭየት ህብረትና ሜክሲኮ ሽልማትን ተቀብለዋል።
በተረፈ የትምህርት ሚኒስትር ዳይረክተር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተከታይ ዳይሬክተር (፲፱፵፪)፣ የብሄራዊ መጻህፍት ቤት ዳይረክተር (፲፱፵፬)ና የካቢኔ ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል።
ክቡር ዶክቶር ከበደ ሚካኤል፥ ኢትዮጵያዊ 'የቀለም ሰው' ኅዳር ፫ ቀን ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. በሰማንያ ሁለት ዓመታቸው አረፉ።
ናሙና ግጥሞች
የተማረ ሆኖ እውነቱን የማይገልጽ ፣ ባለ ጸጋ ሆኖ ገንዘቡን የማይሰጥ፣ ደሃ ሆኖ መስራት የማይሻ ልቡ፣ ሶስቱም ፍሬ ቢሶች፣ ለምንም አይረቡ። | አይነ የለውም አሉ የሰነፍ ልመና ወደ አምላክ ሲጸልይ ማታ በልቦና መንገዱ ሳይመታኝ ባቧራ በጭቃ አድርገኝ ይለዋል ላገሬ እንድበቃ እንጦጦ ተኝቼ ሃረር እንድነቃ | መርዝም መድሃኒት ነው ሲሆን በጠብታ እንዲሁም ለተንኮል አለው ቦታ ቦታ ምን ቢሰለጥኑ ቢራቀቁ በጣም ሁልጊዜ ደጋግሞ ብልጠት አያዋጣም። በጅ የተበተቡት ተንኮል ዞሮ ዞሮ ማጋለጡ አይቀር እጅና እግር አስሮ ። መጽሓፉም ይለናል ሲያስተምረን ጥበብ ብልጥ ሁን እንደባብ የዋህ ሁን እንደርግብ ስለዚህ በብልጠት ተንኮል ስትሰሩ በዝቶ እንዳይገላችሁ ገርነት ጨምሩ ... ከየዕውቀት ብልጭታ የተወሰደ |