peoplepill id: damtew-ayele
DA
Ethiopia
1 views today
1 views this week
Damtew Ayele
Ethiopian singer

Damtew Ayele

The basics

Quick Facts

The details (from wikipedia)

Biography

ዳምጠው አየለ ( 23.11. 1944 አ/ም – 27.10. 2006 አ/ም) ባህላዊ የኢትዮጵያ ዘፋኝ ነበር።

ትውልድና እድገት

በሃምሌ 23 1944 አ/ም ከእናቱ ወይዘሮ ሸዋየ ተካና ከአባቱ አየለ ካሰኝ በመራቤቴ ሰሜን ሸዋ ተወለደ። ልጅነቱን በእረኝነት፥ በግብርና እንዲሁም በቆሎ ተማሪነት እንዳሳለፈ ይናገራል። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ባቅራቢያው በሚገኘው መራኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ተምሯል።

ቤተሰብ

ዳምጠው ህይወቱ እስካለፈችበት ጊዜ ድረስ ለረዥም ጊዜ አብሯት የኖረው ባለቤቱ አልማዝ ይመር ትባላለች። ከአልማዝ ይመር አብዩ ዳምጠውና ቤቴልሄም ዳምጠው የሚባሉ ሁለት ልጆችን አፍርቷል።

የስራ አለም፥ ዘፈንና ዘፋኝነት

ዳምጠው መራቤቴ እያለ በየባእላቱ መዝፈን፣ ማቅራራት እንዲሁም መሸለል ይወድ እንደነበር ተናግሯል። በተለይም ጥምቀትን በማድመቅ ይታወቅ ነበር። የ 6ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ክፍሌ ሞገስ የሚባል መምህሩ ወደ አዲስ አበባ ይዞት እንደመጣ ይናገራል። ባጋጣሚም የምድር ጦር ማስታወቂያ አውጥቶ ስለነበር ይፈተንና ያልፋል። የምድር ጦር ካምፕ ውስጥም እንዲኖር ይደረጋል። የዘፋኝነት ሙያው በዚህ አጋጣሚ ነበር የጀመረው። ዳምጠው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማዉና መነሻ የሆነው አበበ ተሰማ እንደሆነ ይናገራል። ዳምጠው አየለ በምድር ጦር ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል። የኢትዮዽያ ምድር ጦር በ1927 አ/ም ተመስርቶ በ1983 አ/ም የፈረሰ የሙዚቃ ቡድን ነበር። ዳምጠው በመንግስት ለውጥ ምክንያት እስከፈረሰበት ጊዜ ድረስ አብሮ እንደነበር ይናገራል። ምድር ጦርም እያለ ከነታምራት ሞላ፣ ሲራክ ታደሰ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ጥላየ ጨዋቃ፣ ክፍሌ አቦቸር እንዲሁም ሌሎች የጦሩ አባላት ጋር ሰርቷል። ከሌሎች የሙዚቃ ቡድንም ጋር አብሮ ሰርቷል። ለምሳሌ ያክል ከነ ክቡር ጥላሁን ገሰሰ፣ ሙሃሙድ አህመድ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ ሙሉቀን መለስ፣ ፀሃየ ዮሃንስ፣ ቴድሮስ ታደሰ፣ቴድሮስ ካሳሁን እንዲሁም ሌሎችም ጋር ሰርቷል። የዳምጠው አየለ የመጀመሪያ የህትመት ስራው በ1963 አ/ም ሲሆን ወፌ ላላ የሚለው የሸክላ ስራ ነበር። ዳምጠው አየለ ባጠቃላይ 13 ሲዲዎችን ሰርቷል።

እነዚህን ሊንኮች በመጠቆም አንዳንድ ዘፎኖቹን youtube ላይ መመልከት ይችላሉ።

https://www.youtube.com/watch?v=kYnmUcMa7Gg ጎጃም አዘነ

https://www.youtube.com/watch?v=hxbHH9dyK8Y የወሎ ልጅ

https://www.youtube.com/watch?v=aUNKk0GdRgM እንደው ትምቧለል

https://www.youtube.com/watch?v=hmcRQLE1U4A የአባይ ዳር ቆንጆ

https://www.youtube.com/watch?v=m5wCP-5C2dU ደሴ ላይ ከራሄል ዮሃንስ ጋር

https://www.youtube.com/watch?v=1aArxEZ06s8 ለኢትዮጵያ እናቴ


የስደት ኑሮና ህልፈቱ

ዳምጠው አየለ ኖርዌይ ሃገር በስደት ለ 8 አመት ያክል ኖሯል። ኖርዌይ በሚገኘው የኢትዮዽያ ማህበርና እንዲሁም በፓለቲካ ለውጥ ማህበራት ውስጥ በሙያው ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል። ዳምጠው ኖርዌይ በነበረው ቆይታ ከእድሜ እኩያወቹም ሆነ ከወጣቱ ትወልድ ጋር ጥሩ መግባባትና ፍቅር የነበረው አርቲስት ነበር። ዳምጠው ባደረበት የኩላሊት ህመም ምክንያት ኖርዌይ በሚገኙ የህክምና መአከላት ሲረዳ ቢቆይም በሽታው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት ስለሄደ አርቲስት ዳምጠው አገር ቤት ገብቶ ለረዥም ጊዜ የተለያቸውን ቤተሰቦቹን ለማግኘት ይወስናል። ይህንን የአርቲስቱን ውሳኔ ተከትሎ የኢትዮዽያ ማህበር በኖርዌይ ኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮዽያዉያን ጋር በመተባበር ገንዘብ በማሰባሰብ እንዲሁም ከ 250 በላይ ኢትዮጵያዉያን በተገኙበት የክብር ሽኝት አድርጎለታል። የክብር ሽኝት ዝግጅቱን የፕሮግራም ስራዉን ሙሉ በሙሉ የሰራው ኖርዌይ የሚገኘው ያሬድ ባንድ ነበር።

ኢትዮጵያም ከገባ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው በቅ/ገብራኤል ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ 62 አመቱ ሰኔ 27 2006 አ/ም ቀን ህይወቱ አልፏል። የቀብር ስነስርአቱም ወዳጅ፣ ዘመድ እንዲሁም አድናቂዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተፈጽሟል።


ምንጭ

ዳምጠው ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅና

ፀሀፊው ከአርቲስቱ ጋር ያደረገው አጭር ቆይታ

The contents of this page are sourced from Wikipedia article. The contents are available under the CC BY-SA 4.0 license.
Lists
Damtew Ayele is in following lists
comments so far.
Comments
From our partners
Sponsored
Credits
References and sources
Damtew Ayele
arrow-left arrow-right instagram whatsapp myspace quora soundcloud spotify tumblr vk website youtube pandora tunein iheart itunes