Biography
Lists
Also Viewed
The basics
Quick Facts
The details
Biography
ፍሬው ኃይሉ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ተዋናይ እና የግጥምና ዜማ ደራሲ ነው።
የህይወት ታሪክ
ፍሬው ኃይሉ በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. በትግራይ ክ/ሀገር ተንቤን አውራጃ ተወለደ። ቀደም ሲል በድቁና ሲያገለግል የነበረው ፍሬው በ፲፱፻፵፯ ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተቀጠረ። ፍሬው በአኮርዲዮን አጨዋወት ቅልጥፍናው የሚደነቅ ከመሆኑም ሌላ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የተዋጣለት ተዋናይ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ ነበር።
የሥራዎች ዝርዝር
ፍሬው ሀይሉ በሕይወት ዘመኑ ከአንድ መቶ በላይ ዜማዎችን ተጫውቷል። ከተጫወታቸው ዜማዎች በተለይ «ዐይን የተፈጠረው»፣ «እሽሩሩ»፣ «ሱቅ በደረቴ» እና «ኑኑዬ ጨቅላዋ» የተሰኙት ዜማዎች ተወዳጅነታቸው ላቅ ያለ ነው። ፍሬው በ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. አምስት የሚሆኑ የባህል ዜማዎችን በሸክላ አስቀርፆ ለሕዝብ አቅርቧል።